መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን አቅርቦት ከአምራች ወይም አቅራቢ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን አቅርቦት ከአምራች ወይም አቅራቢ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
- ሎት አንድ፡- የዳቦ ዱቄት አቅርቦት (በድጋሚ የወጣ)
- ሎት ሁለት፡- ለእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ግብዓት የሚውል ፕሪሚክስና ሌሎች ተያያዥ ግብዓቶች (በድጋሚ የወጣ)
- ሎት ሶስት፡- የእንሰሳት መኖ መቋጠሪያ ኬሻ ማምረትና ማተም (በድጋሚ የወጣ)
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና አቅራቢዎች አምራች ወይም ኤጀንት ከሆኑ በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሱ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፡-
- ለሎት አንድ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ)
- ለሎት ሁለት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ)
- ለሎት ሶስት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በመገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ስም ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ አስር ሠዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ግዥ ቡድን ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 በኢንተርፕራይዙ ግዥ ቡድን ቢሮ በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓትና ቦታ በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በውስጥ ማስታወቂያ እና በደብዳቤ ይገለፃል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን:- +251912211682 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ
