በአብክመ ኦሮ/ብሄ/ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በከሚሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ስፋታቸው 5,794.84 ካሬ ሜትር የሆኑ ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ እና 154 ካሬ ሜትር ለመኖሪያ በአጠቃላይ 5948.84 ካሬ ሜትር ቦታዎችን በመደበኛ ሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የ2017 1ኛ ዙር መደበኛ ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ኦሮ/ብሄ/ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በከሚሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ስፋታቸው 5,794.84 ካሬ ሜትር የሆኑ ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ እና 154 ካሬ ሜትር ለመኖሪያ በአጠቃላይ 5948.84 ካሬ ሜትር ቦታዎችን በመደበኛ ሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆነ ተጫራቾች ፦
-
የጨረታውን ሰነድ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 700 /ሰባት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቶች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
-
ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 10 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ10 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡
-
ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በአ/ብ/ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ 18/7/ 2017 እስከ 28/7/2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ29/7/2017 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
-
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ30/7/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
-
በጋራ ተደራጅተው /በአክሲዩንን/ ሰነድ ለመግዛት የሚፍልጉ አካለት ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ስምምነት ማረጋገጫ መረጃ
-
ቦታውን ለመጎበኘት ለሚፈልጉ ተጫራቶች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የቅድመ ክፍያውን 30% መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
-
የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨረማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥሮች 09 13 50 18 99 ወይም 09 13 25 99 20 / 0335540255 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ ኦሮ/ብሄ/ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
