Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ያገለገሉ የአስፓልት በርሜሎች በተቀመጠላቸው መነሻ ዋጋ መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ያገለገሉ የአስፓልት በርሜሎች በተቀመጠላቸው መነሻ ዋጋ መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ) ብር በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000322267979 ገቢ በማድረግ ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 (አስር ሺህ) ብር በባንክ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  • አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አስፈላጊውን ሁሉ አሟልተው ንብረቱን በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ የማንሣት ግዴታ አለባቸው።

  • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይዘጋል በዚሁ እለትም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ግዥ ክፍል ይከፈታል።

  • የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡- ዲስትሪከቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

 

ስልክ ቁጥር 025 111-1313 / 09 27 63 61 26/ 09 19 00 80 17 ይደውሉ።

 

 

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

 

 

  

Save Tender