የአ/ከ/ክ/ከ/ወ/05 አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ በግልጽ ጨረታ የተለያዩ ያገለገለ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን እንዲሁም አልጋዎችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2016
የአ/ከ/ክ/ከ/ወ/05 አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ በግልጽ ጨረታ የተለያዩ ያገለገለ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን እንዲሁም አልጋዎችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በአ/ከ/ክ/ከ/ወ/5/ አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 በመምጣት ለሽያጭ የተዘጋጁትን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን እንዲሁም አልጋዎችን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ቀናት ከ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ:: በዚህም መሰረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የማክበርና የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።
የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር)
የተጫራቾች መመሪያ
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን እንዲሁም አልጋዎችን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ05 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በመያዝ በጤና ጣቢያው ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ከዚህ የጨረታ ሠነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ስማቸውን፣ የሚኖሩበት ክፍለ ከተማ፣ወረዳ፣ የቤት ቁጥርና ስልክ ቁጥራቸውን (ተለዋጭ ስልክ ቁጥሮችን ጨምሮ) በመግለጽና በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፡፡ በገዥው ወይም በሕጋዊ ወኪሉ ያልተፈረመ መጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በአንድ መለያ ቁጥር (መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ጽፈው ከፈረሙ በኋላ በኤንቨሎፕ አሽገው የአ/ከ/ክ/ከ/ወ/05 አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቹ በአሃዝ እና በፊደል በሰጠው ዋጋ ልዩነት ካለው አገልግሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ በመውሰድ ያወዳድራል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- ዋጋ ለመስበርና በተለያየ መንገድ ፍትሃዊ ውድድር እንዳይኖር በነጠላ ወይም በቡድን በሚመሳጠሩት ላይ አገልግሎቱ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጥቅል ለተመደቡት ዕቃዎች ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጥቅል እኩል ዋጋ በመስጠት አሸናፊ ቢሆኑ እንደገና በማወዳደር አሸናፊው ይለያል፣ ድጋሚ ተመሳሳይ ዋጋ ከሰጡ አሸናፊው በእጣ እንዲለይ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን ቀድሞ ከሰጡት ዋጋ በማሳነስ መዉዳደር ኢይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት በጥቅል ለተቀመጠው ጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የኢ/ከ/ክ/ከ/ወ/05 አበበ ቢቂላ ጤና ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊ ለሆኑት በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ይታሰብላቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች እና መነሻ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከውድድሩ ሊወጡ አይችሉም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያው በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎት ገቢ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን በ5 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚሰጡት ዋጋ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ወይም ስርዝ ድልዝ ካደረጉ በተስተካከለው ፊት ለፊት መፈረም አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በስሙ ያልገዛ ተጫራች በጨረታው ሊሳተፍ አይችልም፤ ጨረታውን የሚካፈለው በወኪል ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የተሸጠ የጨረታ ሰነድ ተመላሽ አይደረግም፡፡
- ፎቶ ኮፒ በተደረገ የጨረታ ሰነድ የተወዳደረ ተጫራች ከጨረታው እንዲሰረዝ ይደረጋል።
- አንድ ተጫራች ለጨረታ ለቀረቡት ንብረቶች ከአንድ ጊዜ በላይ የጨረታ ሠነድ በማስገባት መወዳደር አይችልም፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118279062/01127332081 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ
