የኢትዮጵያ ፖስታ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግጨ 23/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፖስታ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- የመኪና መለዋወጫዎቹን ለመጫረት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በድርጅቱ ገንዘብ ቤት 2ኛ ፎቅ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን 2ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ለመኪና መለዋወጫዎች የጨረታ ማስከበሪያ በቅድሚያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በጨረታው መዝጊያ ቀን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 27/2017 ዓ.ም በድርጅቱ የሠራተኞች ክበብ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፋባቸው የመለዋወጫ ዕቃዎች በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን በተገለፀው ቀናት ውስጥ ካላነሱ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ይወረሳል፡፡
- እያንዳንዱ የመኪና መለዋወጫ በተናጠል የሚሸጥ ይሆናል፡፡
- መለዋወጫዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሰነዱን ከገዙበት ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ሲሆኑ በመካከላችን በሚፈጸም ሕጋዊ ውል መሠረት ይከናወናል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት /ለበለጠ መረጃ 0911954537
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት
