ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስድስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ ከተባለ አጋር ድርጅት ጋር በመሆን "Mobile Toolkit for Climate Resilience" የሚል ትኩረቱን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያደረገ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በነዚህ አጋር ትምህርት ቤቶች ላይ የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ለሚሰሩ ሥራዎች ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመግዛት አቅደዋል፡፡ በመሆኑም ቀጥሎ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ቁሳቁሶቹን ማቅረብ የምትችሉ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስድስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ ከተባለ አጋር ድርጅት ጋር በመሆን "Mobile Toolkit for Climate Resilience" የሚል ትኩረቱን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያደረገ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በነዚህ አጋር ትምህርት ቤቶች ላይ የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ለሚሰሩ ሥራዎች ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመግዛት አቅደዋል፡፡ በመሆኑም ቀጥሎ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ቁሳቁሶቹን ማቅረብ የምትችሉ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡ ሎቶቹም፡-
- Lot 1: ለቆሻሻ አወጋገድ የሚውሉ (Waste Management materials)
- Lot 2:- የውሃ ታንከር ከነአክሰሰሪው (Water tanker with accessories)
- Lot 3:- የተለያዩ የእርሻ መሣሪያዎች እና የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘሮች (School Gardening)
- Lot 5:- የክበባት ቁሳቁሶች (Club Materials)
- Lot 6:- ለአየር ንብረት ለውጥ አምባሳደሮች አንጸባራቂ (ሰደሪያ) (Pips)
- Lot 7- ተንቀሳቃሽ ሳጥን (የተለያዩ የአየር ንብረት ሰነዶችን እና ቁሳቁሶችን መያዣ) (Mobile toolkit Box) በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶችም:-
- በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ቲን ነምበር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የቫት /ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እንዲሁም
- ቁሳቁሶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ፣ የእቃዎቹን ጥራት ሳምፕል አቅርበው ማሳየት የሚችሉ እና ለእቃዎቹ ጥራት ዋስትና መስጠት የሚችሉ፣
- ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ስቶር ማድረስ የሚችሉ፣
- በ Ethiopian Center for Development /ECD/ ስም የተዘጋጀ የ25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ የማስያዣ ዋስትና (CPO) ማቅረብ የሚችሉ፣
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት እለት አንስቶ ለ7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት ECD/ ቢሮ በመምጣት የጨረታውን ሰነድ በነጻ በመውሰድ ቁሳቁሶቹን የምታቀርቡበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ገቢ አድርጋችሁ እንድትወዳደሩ እንገልፃለን፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ አለም ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ:- 0982 88 28 26
ማሳሰቢያ፦ ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲቨሎፕመንት /ECD/
