የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በዩኒሴፍ የልዩ ፍላጎት /አካቶ/ ትምህርት ድጋፍ መስጫ ማዕከላት ቁሳቁስ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የሚኒሚዲያ ክበባትን ለማጠናከር የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች እና ሌሎች ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 08 ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትም/ቢሮ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በዩኒሴፍ የልዩ ፍላጎት /አካቶ/ ትምህርት ድጋፍ መስጫ ማዕከላት ቁሳቁስ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የሚኒሚዲያ ክበባትን ለማጠናከር የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ግዥ ማለትም
- ለተቋቋሙት 4 የልዩ ፍላጎት /አካቶ/ ትምህርት የድጋፍ መስጫ ማዕከላት ማቋቋሚያና ማደራጃ የሚውሉ የልዩ ትምህርት ቁሳቁሶችና የአካል ድጋፍ መስጫ መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የሞንቶሶሪ ኪቶችና ሼልፎች ግዥ
- የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የሚኒሚዲያ ክበባት የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ግዥ ለመፈጸም በሥራ መስክ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃዳቸውንና የምዝገባ ሰርተፊኬታቸውን ያሳደሱ በግብር ከፋይነት ተመዝግቦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፤ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበት መረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች ትምህርት ቢሮ ቁጥር 18 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱን ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘውትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ዶክመንት ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻ አሽጎ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮ ቁጥር 18 ለዚህ በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ የሚገልጽ ለተቋቋሙት የልዩ ፍላጎት /አካቶ/ ትምህርት የድጋፍ መስጫ ማዕከላት ማቋቋሚያና ማደራጃ የሚውሉ የልዩ ትምህርት ቁሳቁሶች የገንዘብ መጠን ብር 30,000.00 /ሠላሳ ሺህ ብር/ ጨረታ ማስከበሪያ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የሚኒሚዲያ ክበባት የኤሌክትሮኒክስ -ቁሳቁስ ግዥ የገንዘብ መጠን ብር 20,000 00 /ሃያ ሺህ ብር/ ጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጧቱ 2፡30- 5፡00 ሰዓት ሰነዱ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ገብቶ ወዲያውኑ 5፡00 ታሽጎ ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0467752359/0916863055/ መጠየቅ ይችላሉ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ
ጂንካ
