የኢትዮጵያ ፖስታ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ራክ /Back እና የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ /Divider/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግጨ 24/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፖስታ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ራክ /Back እና የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ /Divider/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የማስረጃውን ፎቶ ኮፒ በማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች በድርጅቱ ገንዘብ ቤት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል እየቀረቡ የጨረታ ሠነድ በመውሰድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በማለት ለየብቻ (በተናጠል) በመለየት በጨረታ ሠነዱ ላይ በዝርዝር በተገለጸው የሥራ ትዕዛዝ /እስፔስፊኬሽን/ መሠረት ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ እስከ ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ሠነዱን ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች በቅድሚያ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) 15,000.00 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ዶክመንት ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 27 ቀን 2017ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የሠራተኞች ክበብ ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911954537 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ
