በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፐ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ለፒቪሲ ምርት ማምረቻ የሚሆን ፒቪሲ እና ስታብላይዘር ጥሬ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፐ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ለፒቪሲ ምርት ማምረቻ የሚሆን ፒቪሲ እና ስታብላይዘር ጥሬ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በኢንዱስትሪው ሰፐላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምነት ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ የኢንዱስትሪ ሰፐላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቹ የዕቃዎችን የተናጥል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ትክክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መግለፅ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፤ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
- ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በፁሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥራችን 0116670485/0118592286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየ ገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የቫት ሠርተፊኬት፣ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ ሠርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡- በመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
አዲስ አበባ
