በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በዞኑ ለሚገኘው ኮሚኒኬሽን መምሪያ አገልግሎት የሚውል የሚዲያ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 10/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በዞኑ ለሚገኘው ኮሚኒኬሽን መምሪያ አገልግሎት የሚውል፡-
የሚዲያ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዢው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራቹን ስም፤ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ ከሆነ 60 እና ከዚያ በላይ ቀናት የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በጉ/ዘ/7/ባ/ዋ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ግዥ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 18 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጂናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 18 በይፋ ይከፈታል፣
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-3-30-01-12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊዎች ላቀረቡት እቃዎች የእጅ በእጅ ደረሰኝ ተጠቃሚ ከሆኑ ከገቢዎች የማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት እንገልፃለን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ
