የመብራት መቆጣጠሪያ ዕቃ /AVR (Automatic Voltage Regulator WITH accessories የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚድያ ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
1. የመብራት መቆጣጠሪያ ዕቃ /AVR (Automatic Voltage Regulator WITH accessories የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚድያ ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ቁጥር 002/2017
የመብራት መቆጣጠሪያ ዕቃ /AVR (Automatic Voltage Regulator) WITH accessories ዕቃ ግዥ በዚሁ መሰረት በጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገበበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ቲን ነምበር ምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጳውሎስ ሆስፒታል ቢታንያ ክሊኒከ ገባ ብሎ በመሄድ በ100 ብር ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ቢድ ቦንድ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ስም ሞልተው ከኦርጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 2 /ሁለት/ ኮፒ እንዲሁም የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 2 /ሁለት ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በትክክል መቅረብ አለበት የኮፒ ሰነዶች በአይነትም ሆነ በብዛት ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። ጨረታውን በ16ኛው ቀን እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ ተወዳዳሪ ድርጅቶች ጨረታውን ሞልተው አዲስ አበባ በሚገኘው የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጳውሎስ ሆስፒታል ቢታንያ ክሊኒክ ገባ ብሎ በሚዘጋጀገው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 0910000329፤ 0928653853፤ 0912 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚድያ
