በጉምሩከ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ያገለገሉ ዕቃዎች ሎት -1-ሲስተም ዩኒት ፤ ሞኔተር ሎት 2 ተመላሽ የመኪና መለዋወጫ ፣ ሎት -3 -ተመላሽ ቶነሮች እና ያገለገሉ ተሽከርካሪ ወንበሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2017
በጉምሩከ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ያገለገሉ ዕቃዎች ሎት -1-ሲስተም ዩኒት ፤ ሞኔተር ሎት 2 ተመላሽ የመኪና መለዋወጫ ፣ ሎት -3 -ተመላሽ ቶነሮች እና ያገለገሉ ተሽከርካሪ ወንበሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመስከቱትን ነጥቦች በማሟላት መጫረት የምትችሉ መሆን እንገልፃለን።
- አግባብነት ያለው ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ክፍያ ምስክር ወረቀት እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና እንደአስፈላጊነቱ ሌላ ተፈላጊ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቱ ካርጎ ተርሚናል 1ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍለው የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶችን በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ግቢ ውስጥ እና አይካስ በሚገኘው ጉምሩክ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ያገለገሉ ንብረቶችን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ 5000.00 (አምስት ሺ ብር) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውስጥ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፣
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0116651351/ 0116651386 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ለመቀበል ወይም በሙሉ ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻ፡-
በቦሌ ሚካኤል መንገድ በካርጎ ቅጥር ግቢ ውስጥ የጉምሩክ ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን ቢሮ
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
