በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃላ/የተ/ አሰላ ብቅል ፋብሪካ ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የብቅል ምርት እና ተረፈ ምርት መቋጠሪያ ከረጢት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል።
ለ 3ኛ ጊዜ የወጣ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: NCB/OACFLTD/AMF/11/2017
በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃላ/የተ/ አሰላ ብቅል ፋብሪካ ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የብቅል ምርት እና ተረፈ ምርት መቋጠሪያ ከረጢት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡-
- ተጫራቾች የ2017 የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል ገቢ በማድረግ/፡
- ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 2፡00-6:00 ከሰዓት በኋላ 7:00-10:00 ሰዓት ድረስ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወሰደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ-ቁሉምሳ ከሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 003 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከታች ከተጠቀሰው የመዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ፖስታቸውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በተቀመጠው ዝርዝር መስፈርት መሰረት ሶስት ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን -
ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 11 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ12ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ለመገኘት በሚሹ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት የአሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ 7ኛ (ሰባተኛ) ፎቶ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፣ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር:- 09-65-65-04-81/09-65-65-02-85 /022331 1799 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ
