Tender Detail

Tender Details

  • Company BRANNA PRINTING ENTERPRISE (ብራና ማተሚያ ድርጅት)
  • Address ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114 42 64 80
  • Website
  • Deadline08 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር አምስት መቶ (500.00)
  • opening dateበ11ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Categories Packaging And Labelling , Plastic Raw Materials And Products , Printing And Publishing

ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ የህትመት ጥሬ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ የህትመት ጥሬ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

1ኛ በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ፣

2ኛ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

3ኛ የግብር ከፋይነት መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣

4ኛ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣

5ኛ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣

6ኛ በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ ገፅ በአቅራቢነት ተመዝጋቢና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

7ኛ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር አምስት መቶ (500.00) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ወሎ ሰፈር በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 26 በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

8ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 2% በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣

9ኛ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስረከቢያ ጊዜውን መጥቀስ አለባቸው፣

10ኛ ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ድርጅቱ መጋዘን ድረስ ማድረስ አለባቸው፣

11ኛ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛው የሥራ ቀን እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

12ኛ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል

ስልክ ቁጥር፡- 011-412-1664

 

ብራና ማተሚያ ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Branna Printing Enterprise seeks bids from local suppliers for various printing raw materials. Bidders must hold valid trade registration, business license, tax clearance, VAT certificate, and supplier registration with the Public Procurement Agency. Delivery to the enterprise warehouse is required.
Save Tender