በአብከመ የጎንደር መም/ትም/ኮሌጅ ለጎንደር ትምህርት መሳሪያዎች ክዘናና ስርጭት ማእከል የመኪና መለዋወጫ እቃ ለ2ኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብከመ የጎንደር መም/ትም/ኮሌጅ ለጎንደር ትምህርት መሳሪያዎች ክዘናና ስርጭት ማእከል የመኪና መለዋወጫ እቃ ለ2ኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሚመለከተው የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
- የግዥው የብር መጠን 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለበት ለዚህም ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከዚህ በፊት በተሰጣቸው የእቃ አቅርቦት ወይም አገልግሎቶች ችግር ኖሮባቸው በየደረጃው በተቀመጠው እግባብ ባለውና በሚመለከተው አካል እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ከ1 እስከ 4 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 ብር በመክፈል ከ24/09/2017 ዓ/ም እስከ 08/10/2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠ/ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በአማርኛ የተተረጎመ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለበት። በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ በውስጥ ገቢ ደረሰኝ መቁረጥ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ በጎንደር መም/ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት ከ24/09/2017 ዓ.ም እስከ 09/10/2017 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት ጎ/መ/ት/ኮ ቢሮ ቁጥር G -1 በ09/10/2017 ዓ.ም በ3፡35 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ኮሌጁ ቫት ሰብሳቢ በመሆኑ የቫት ሂሳብን 7.5% ቆርጠን የምናስቀር መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ጎ/መ/ት/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር G1 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0581121634 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
