በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በከሚሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ለድርጅት 3,527.94 ካ.ሜ እና ለመኖሪያ 210.39 ካ.ሜ ጠቅላላ ስፋታቸው 3,738.33 ካሬ ሜትር የሆኑ ለመኖሪያና ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ለ2017 ዓ.ም 2ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በከሚሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ለድርጅት 3,527.94 ካ.ሜ እና ለመኖሪያ 210.39 ካ.ሜ ጠቅላላ ስፋታቸው 3,738.33 ካሬ ሜትር የሆኑ ለመኖሪያና ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መስፈረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች:-
- የጨረታውን ሰነድ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 20 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡ እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ተጫራቾች የቅድመ ክፍያ ከጠቅላላው ብር ላይ 30% መክፈል የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎችን ለመለየት የሚከተሉትን የማወዳደሪያ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ ይሆናል፡-
ሀ) ተጫራቾች ለቦታው ያቀረቡት ዋጋ 80%
ለ) የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን 20% የሚያዝ ይሆናል
- ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ09/10/2017 ዓ.ም እስከ 20/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ 20/10/2017 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 21/10/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በጋራ ተደራጅተው /በአክሲዮን/ እነ በሚል ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ አካላት ከሚመለከተው አካል እነ የተባላችሁበትን ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መረጃ በስም ዝርዝር ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።
- የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/ 2014 መሰረት በማድረግ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0913501899/0335540255/0913259920 ወይምንም Gmail address:- Ke.ketemaaglglot@gmail.com መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
