የፌደ/ማ/ቤት ኮሚሽን ንብረትነታቸው የኮሚሽኑ የሆነና በተለያዩ ማዕከላት ተከማችተው የሚገኙ ቁርጥራጭ የብረታ ብረትና የብረታ ብረት ውጤቶችን ባሉበት ሁኔታ ከፌደራል የገንዘብ ሚ/ር የተሰጠ የመነሻ ዋጋን መሰረት በማድረግ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የፌደ/ማ/ቤት ኮሚሽን ንብረትነታቸው የኮሚሽኑ የሆነና በተለያዩ ማዕከላት ተከማችተው የሚገኙ ቁርጥራጭ የብረታ ብረትና የብረታ ብረት ውጤቶችን ባሉበት ሁኔታ ከፌደራል የገንዘብ ሚ/ር የተሰጠ የመነሻ ዋጋን መሰረት በማድረግ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው ላይ የሚወዳደሩት በማዕድን ሚ/ር የተለዩ ብረት አቅላጭ የባለ ድርጅት የሆኑና የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና መታወቂያ ማቅረብ የሚችሉ ናቸው።
- ተጫራቾች ፒያሳ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አጠገብ በሚገኘው የፌደራል ማ/ቤት ኮሚሽን 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 ገዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የብረቶቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራጮች መመረያና የዋጋ ማቀረቢያ ቅፅ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከቢሮ ቁጥር 105 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብረታ ብረቶቹን ከፍተኛ ጥበቃ ማረ/ማዕከል (ገሳን)፣ ድሬደዋ ሁሉ አቀፍ ማረ/ማረ/ማዕከልና ማረ/ፖሊስ ማስ/ተቋም (አሌልቱ) መሆኑን ተገንዝባችሁ ንብረቶቹ ያሉበትን ሁኔታ በአካል ተገኝቶ መመልከት የሚቻል ሲሆን ለምልከታው ቀድማችሁ ኘሮግራም በማስያዝ የንብረቶቹን ይዞታ ማየት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናስገነዝባለን።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ቁርጥራጭ የብረት ዓይነት የጨረታ መነሻ 10 (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከመዝጊያው ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተዘጋጀ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል። ይሁን እንጂ የብረታ ብረቶቹን ግምታዊ ጠቅላላ ዋጋ 10 (አስር በመቶ) ዋስትና ያላስያዘ እንዲሁም በሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
- የጨረታ ማስገቢያ ሣጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የግዥ/ን/አስተዳዶክቶረት ቢሮ ቁጥር 407 ይከፈታል። ነገር ግን በጨረታው መክፈቻ ቀን ኮሚሽኑን አቅም በላይ የሆነ ጉዳይ ከገጠመው ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ጨረታው እንዲከፈት ይደረጋል። ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በብሔራዊ በዓል ቀን የጨረታ ስነ-ስርዓት አይኖርም። ይሁንና ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን አከፋፈት ስነስርዓት አያስቀረውም።
- ጨረታውን አሸናፊ የሆኑ ተጫራጮች ለሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው 7(ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ በ5(አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ሙሉ ክፍያ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል። ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ውርስ ተደርጎ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ይደረጋል።
- ጨረታውን አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን ብረታ ብረቶች ሙሉ ክፍያ ፈፅመው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገm ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያሸነፋትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ የሚዛንና ሌሎች መጪዎችን በመሸፈን ብረታ ብረቱ ከሚገኝበት ስፍራ ቅርብ በሆነ የመንግስት የምድር ሚዛን በማስመዘን ኘሪንትአውት በማቀርብ ውል በፈረሙ በ15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶቹን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው። ግምታዊ መጠኑ ከኘሪንትአውት ከሚገኘው ትክክለኛ የብረቱ መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት የሚኖረውን ልዩነት ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን ገዥው በትርፍ የሰጠው ገንዘብ ካለ በኮሚሽኑ ተመላሽ ይደረጋል።
- ኮሚሽኑ ያመጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራቾ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ15(አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ወይም ሌላ ጨረታውን ለመሰረዝ የሚያበቃ ምክንያት ካጋጠመው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ፒያሳ ፌደራል ማ/ቤት ኮሚሽን ዋ/መ/ቤት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 011-126 4844/ 09-23-27-37-67/07-05-27-37-67 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ቴሌ 011-126-5670 ፋክስ - 011-126-5418 Po. Box 22 37 አ/በባ-ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
የፌደ/ማ/ቤት ኮሚሽን
