የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 018/18
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ አንድ (ሎት 1) ፡- ለሁለት አመት የሚቆይ የመነፅር ስራ አገልግሎት ግዥ።
በጨረታ ሁለት (ሎት 2) ፡- ለሁለት አመት የሚቆይ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች ፍተሻ፣ ሙሌትና የመለዋወጫ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ።
በጨረታ ሶስት (ሎት 3) ፦ ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ የሚገኘውን የድርጅቱ ይዞታ (መርሃ ጥበብ ቅርንጫፍ መ/ቤት) ለንግድ አገልግሎቶች ማለትም ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሱቆች ወዘተ ስራዎች ሊጠቀሙ ለሚችሉ ድርጅቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
በጨረታ ሶስት (ሎት 4) - የህትመት ውጤቶች ከቦታ ቦታ ማጓጓዣ ጋሪ (ድርጅቱ ውስጥ በመገኘት የሚፈልገውን ስራ አይቶ ዲዛይን ሰርቶ በማቅረብ የወረቀት ማጓጓዣ ጋሪዎቹን መስራት) አገልግሎት ግዥ።
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታከስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።
ጨረታው 19/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴከኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-155-5230
ድረ ገፅ (www.ethbspe.org (http://www.ethbspe.org/) )
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
