Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በሐራጅና ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 17/2017 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ /ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በሐራጅና ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ . 17/2017 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

/

ዘርፍ

የጨረታው ዓይነት

እቃው ያለበት ቦታ

1

አልባሳት

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

2

ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

3

ኮስሞቲክስ

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

4

ፕላስቲክ ሸራዎች

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

 

በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-

  1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ከሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡ በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፤
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት 100-500 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ /ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ //ቤት ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 30 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በቅ//ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

 

/

የቅ//ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ሰመራ ///ቤት

ግልጽ ጨረታ

እስከ 19/10/2017

20/10/2017 / 330 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 345 ሰዓት ይከፈታል

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፦ በሰመራ ///ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
  2. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጽ 3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ 5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
  4. //ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
  5. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ፡- 033 366 2302/033 366 5004 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ //ቤት

 

Save Tender