Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሰመራ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0335590114
  • Website
  • Deadline28 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-06-28 00:00:00
  • Categories Spare Parts , Electronics Materials , Cosmotics

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስፔርፓርት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ ዕቃዎች በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 54/2017 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢ... ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ //ቤት ስፔርፓርት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ ዕቃዎች በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ . 54/2017 . እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

  1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ለሐራጅ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት 200-600 ሰዓት ከሰዓት በኋላ 900-1200 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ /ቤቱ በመገኘት፤ ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ለምድቡ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እንዲሁም በሐራጅ ጨረታ ለወጡት ዕቃዎች ለእያንዳንዳቸው 100,000 (መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በጋላፊ ጉምሩክ //ቤት ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1.

ጋላፊ ጉምሩክ //ቤት

ሐራጅ ጨረታ

እስከ 21/10/2017

21/10/2017 . 300 ሰዓት ይከፈታል።

 

 

 

 

 

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ///ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጅናል ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ 3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  3. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ 05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈላው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
  4. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 033 559 0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ //ቤት

 

Save Tender