በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የምግብ እህል፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ በርበሬ ቅመማ ቅመም እና የማገዶ እንጨት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የምግብ እህል፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ በርበሬ ቅመማ ቅመም እና የማገዶ እንጨት አቅርቦት ለስድስት ወር ማለትም ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ/ም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ማስረጃ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ መሆኑን፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ በብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር / መ/ቤቱ የአዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሕጋዊ የምግብ እህል ሽቀጣ ሸቀጥ፣ በርበሬ፣ ቅመማ ቅመም እና የማገዶ እንጨት ለእያንዳንዱ የንግድ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ፖስታውን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመምሪያው ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ25/10/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/11/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ መሆኑንና ጨረታው በዚሁ እለት በ 09/11/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት፡፡
- አሸናፊው በየወሩ እንደ ሕግ ታራሚዎች ብዛት አቅርቦቱ ሊጨምር ሊቀንስ የሚችል ሲሆን እንዲቀርብ መምሪያው በሚገልፀው መጠን በየወሩ የሚቀርብ መሆኑን እና አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የውድድሩ ሁኔታ በተናጠል በየዘርፉ በነጠላ የሚወዳደሩ መሆኑን እና ተቋሙ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ይከፈታል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ካስፈለገዎት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም በስልክ ቁጥር 011 681 17 92 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን።
የሰ/ሽዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ
