የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሰራተኞች መዝናኛ ክቡብ (ካፌ) ገብቶ የሚሰራ ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት አመት የሚቆይ አገልግሎት የሚሰጠውን ብቁ አቅራቢ/አገልግሎት ሰጪ ይፈልጋል።
የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የመስተንግዶ አገልግሎት የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- ECCGB/NCB/004/2017
የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥበት የኢትዮጵያና ጅቡቲ ኮሪደር ላይ የሚገኝ እና ከ90% በላይ የአገሪቱ የገቢና ወጭ ትራንዚት የሚፈጸምበት በመሆኑ ከቅርንጫፍ ሰራተኞቹ በተጨማሪ በርካታ የምግብና የመጠጥ አገልግሎት ፈላጊ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸው ይታወቃል። በመሆኑም መዝናኛ ክበቡ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች፣ ለፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ ለአጋዥ ሰራተኞች እንዲሁም ከሌሎች ቅርንጫፍ ለድጋፍ ከሚመጡ የተቋሙ ሰራተኞች ውጪ ላሉ ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት ይቻል ዘንድ በቅ/ጽ/ቤቱ ሚገኘውን የሰራተኞች መዝናኛ ክቡብ (ካፌ) ገብቶ የሚሰራ ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት አመት የሚቆይ አገልግሎት የሚሰጠውን ብቁ አቅራቢ/አገልግሎት ሰጪ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ውስጥ የሚገኘው የሰራተኞች ክበብ ውስጥ ገብተው አገልግሎትና አቅርቦት ሲሰጡ ቅ/ጽ/ቤቱ የነጻ የቤት ኪራይ ፤ የውሃ የመብራት፣ ደረጃውን የጠበቀ ወንበርና ጠረጴዛ በነጻ የሚያቀርብ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
- የጨረታውን ሰነድ በጋዜጣ ላይ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋት 2፡30- 6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ቅዳሜን ሳይጨምር ከ 9፡00 -12፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሃብት አስተዳደር የስራ ሂደት ግዥና ፋይናንስ ቡድን መውሰድ ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በ2017 የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ ቫት ተመዝጋቢ (ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርፍኬት) ፤ በአቅራቢነት ምዝገባ (Supplier list) የተመዘገበና ማስረጃ የሚያቀርብ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ በባንክ የተመሰከረለት C.P.O (GALAFI CUSTOMS BRANCH OFFICE) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታው ሳጥን ከመዘጋቱ በፊት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ፤ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን እንዲሁም ድርጅት ከሆነ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ አሟልተው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የክበቡን አገልግሎት የሚያቀርቡበትን ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይንም ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን 27/10/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሃብት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ግዥና ፋይናንስ ቡድን በመሄድ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታው ሳጥን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአገልግሎት ወይም የአቅርቦት ዋጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሰበረ ዋጋ ሆኖ ካገኘው ከጨረታ ውድድር ውጪ የሚያደርግ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናቶች ውስጥ ውሉን መፈጸም አለባቸው። ይህ ሳይሆን ቢቀር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃውን ጨረታ ሰነዱ ላይ ይመልከቱ።
ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0913 42 35 13 ፣ 0939 87 73 75 ፣ 0925 50 11 09 እና 0930 88 15 81 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
