በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስማድል ኮሚውኒኬሽን ተርሚናል ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለአለበት ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 መገናኛ አካባቢ አምቼ ፊት ለፊት ለዋና አስፓልት መንገድ በጣም ቅርብ በሆነ ቦታ ላይ የሚገኘውን G+4 መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ (ለሁለተኛ ጊዜ) የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መ/ቤት ቁጥር 2/2017
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስማድል ኮሚውኒኬሽን ተርሚናል ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለአለበት ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 መገናኛ አካባቢ አምቼ ፊት ለፊት ለዋና አስፓልት መንገድ በጣም ቅርብ በሆነ ቦታ አክሰስ ሪል እስቴት እና እሳት አደጋ መከላከያ መካከል የሚገኝ የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000060502305 የሆነ G+4 መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልፅ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል።
- በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ቤት የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) “በጉምሩክ ኮሚሽን አ/አ/ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት" (CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOMS BRANCH OFFICE) ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚከተለው ጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀን |
|
1 |
አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000060502305 የሆነ G+4 መኖሪያ ቤት |
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት |
ማስታወቂያ በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡15 ሰዓት ይከፈታል። |
- የጨረታ መክፈቻ ቦታ ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር ቅርጥ ግቢ የጨረታ አዳራሽ/ የሠራተኞች ካፌ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
- የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደአስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረስ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የቤት ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች ሻጭን አይመለከትም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፉበትን ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ. 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 68 45 37 እና 0116 68 41 93 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
