አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ቁጥር 2 ላፍቶ ሁለገብ ገበያ ማእከል ያስገነባቸውን ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ ድርጅቶች ንግድ ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን በክፍያ ማስተላለፍ ይፈልጋል ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ዓይነት፡ ለካፍቴሪያ አገልግሎት የንግድ ቤት
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ቁጥር 2 ላፍቶ ሁለገብ ገበያ ማእከል ያስገነባቸውን ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ ድርጅቶች ንግድ ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን በክፍያ ማስተላለፍ ይፈልጋል ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩና የጸና የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
- ለካፍቴሪያ አገልግሎት ስለመመዝገባቸው እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000 (ሃምሳ ሺ ብር) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ስም ሲፒኦ (ጋራንትድ ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ቢሮው በሰጣችሁ ፎርማት ላይ በመሙላት የድርጅታችሁን ስም፣የኃላፊ ስምና ፊርማ በማህተም አስደግፋችሁ ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ፣
- ፋይናንሻል አንድ ኦሪጂናል እና ፋይናንሻል አንድ ኮፒ
- ቴክኒካል አንድ ኦሪጂናል እና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኃል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ንግድ ቢሮ የግዢ ዳሬክቶሬት 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር- 011 812 6179/ 011 170 3024 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደጃች ውቤ 1888 ህንጻ 8ተኛ
ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ
