አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ልዩ ስሙ ላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማእከል ውስጥ ያስገነባቸውን ለባንክ አገልግሎት የሚውል የንግድ ቤት መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ክፍያ ማስተላለፍ ይፈልጋል ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ዓይነት፡- ለባንክ አገልግሎት መስጫ ቢሮ
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ልዩ ስሙ ላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማእከል ውስጥ ያስገነባቸውን ለባንክ አገልግሎት የሚውል የንግድ ቤት መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ክፍያ ማስተላለፍ ይፈልጋል ።
- በዘርፉ የተሰማራና በብሄራዊ ባንክ እውቅና ያለው የጸና የንግድ ስራ ፈቃድ ያላው፣
- በገበያ ማዕከሉ ለሚገኙ አምራቾችና ሸማቾች ቀልጣፋ ዘመናዊና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት የሚችል ።
- ከአምራቾች ፣አርሶአደሮች ጋር በቅርበት ስለመስራቱ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1000000 (አንድ መቶ ሺ ብር) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ስም ሲፒኦ (ጋራንትድ ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ የሚችሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ቢሮው በሰጣችሁ ፎርማት ላይ በመሙላት የድርጅታችሁን ስም፣የኃላፊ ስምና ፊርማ በማህተም አስደግፋችሁ ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ፣
- ፋይናንሻል አንድ ኦሪጂናል እና ፋይናንሻል አንድ ኮፒ
- ቴክኒካል አንድ ኦሪጂናል እና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2:30 እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ንግድ ቢሮ የግዢ ዳሬክቶሬት 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኃል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 812 6179/ 011 170 3024 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደጃች ውቤ 1888 ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ
