በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ጽ/ቤቶች በ 2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የሰራተኛ ካፌ መስተንግዶ ከነሙሉ እቃው ጋር እንዲሁም የሠራተኞች የውስጥ መስተንግዶ ፣ የህትመት ስራዎች የትራንስፖርት አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ 001/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ጽ/ቤቶች በ 2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የሰራተኛ ካፌ መስተንግዶ ከነሙሉ እቃው ጋር እንዲሁም የሠራተኞች የውስጥ መስተንግዶ ፣ የህትመት ስራዎች የትራንስፖርት አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
በጨረታው መወዳደር የሚችሉት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በሚያመርቱት ምርት ብቻ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ
ሎት 1 መስተንግዶ 3,545.00
ሎት 2 ትራንስፖርት 3,000.00
ሎት 3 የሠራተኞች ካፌ ከሙሉ እቃዎች ጋር 21,186.00
ሎት 4 ህትመት 5042.00
- የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እሸት ት/ቤት ጀርባ የወረዳ 09 አስተዳደር 2ተኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ለተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ሰነድ ማስገባት ይቻላል። (በ10 ቀን 17/1/2017 (በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜና እሑድ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋ/ጽ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የጨረታ ሳጥን በ11ኛው ቀን ጨረታው 3፡30 ታሽጎ በዚያኑ ቀን 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ፍሉድ ያለበት ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በወሰዱት በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ በመፈረም እና ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፋይናሻል እና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ በየሎቱ ለዮበቻ በማሸግ በወረዳው አድራሻ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10 ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል
- በጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ እና ማህተም የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
- ተጫራቾች ያለፉበትን እቃዎች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ግምጃ ቤት በራሳቸው ትራንስፖርት ማድረስ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩበት ዝርዝር እቃዎች መሰረት ናሙናውን አስቀድሞ ማቅረብ አለባቸው ጨረታ ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫት ተጨምሮ መሙላት አለባቸው ይህ ካልሆነ ተቀባይነት የለውም
- አነስተኛና ጥቃቅን በሚያመርቱት ምርት ብቻ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ በማያመርቱት ምርት ላይ ግን እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
አድራሻ፡-
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ኳስ ሜዳ እሸት ት/ቤት ጀርባ ወረዳ 9 አስተዳደር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-2-30-41-01 / 011-2-75-90-43
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት
