በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሃብሄር ጉዳይ ችሎት በአዳማ ከተማ ደምበላ ከ/ከተማ ኢሬቻ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውን ቤት በጨረታ አወዳድሮ የሚሸጥ መሆኑን እየገለጽን መግዛት የሚፈልጉ ቀርባችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/አ/ባለ መብት ምህረት ሃይሉ እና ፍ/ባለ እዳ ፍጹም ሃይሉ 6 ሰዎች መካከል የሚገኝ የአፈጻጸ ክርክር አስመልክቶ፡ የካርታ ቁጥር 619/83 እና የቤት ቁጥር 921 የሆነ በሟች አቶ ሃይሉ አያና ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በአዳማ ከተማ ደምበላ ከ/ከተማ ኢሬቻ ወረዳ ውስጥ ስፋቱ 300 ካ.ሜ ላይ የሚገኝ በባለሞያ ቀረበ ግምት ብር 3,640,816.39 /ሶስት ሚሊየን ስድስት መቶ አርባ ሺህ ስምንት መቶ አስራ ስድስት ከ 39/100 ሳንቲም/ መነሻ ዋጋ በማድረግ ግልጽ በሆነ ጨረታ በቀን 17/12/2017 3፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ቤቱ በሚገኝበት የጨረታ ኮሚቴው በመግዛት ለሚፈልጉ ሰዎችን ድርጅቶችን አወዳድሮ የሚሸጥ መሆኑን እየገለጽን መግዛት የሚፈልግ ቀርባችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው ከቀን 16/11/2017 እስከ 16/12/2017 ለተከታታይ 30 ቀናት በቤቱ በር እና አጥር ላይ በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አጥር፣ በኢሬታ ወረዳ አስተዳደር በቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ፣ ውስ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ ሰፊው ማህበረሰብ ሊገኝ የሚችልበት ቦታ እና በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- መግዛት የሚፈልግ ሰው /ድርጅት/ የግምቱን ገንዘብ ብር 3,640,816.39 /ሶስት ሚሊየን ስድስት መቶ አርባ ሺህ ስምንት መቶ አስራ ስድስት ከ 39/100 ሳንቲም/
- 1/4 ሲ.ፒ.ኦ ገቢ ማድረጉን የባንክ ማስረጃ (እስሊፕ) ማቅረብ አለበት፡፡
በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሃብሄር ጉዳይ ችሎት
