የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ኦብሶሌት የውሃ ፓምፖች መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ECWCT/NCB/SG-01/2018
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ኦብሶሌት የውሃ ፓምፖች መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በማቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም ገዥ ክፍት ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር አስር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ጋራንቲ (የባንክ ዋስትና) ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ መምሪያ-1 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ሃምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ መምሪያ-1 የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ
አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 011 896 2991
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን
