የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አስ/ዲ/ግ/ሥ/ቢሮ 005/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም-
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን ጨረታ ለመሳተፍ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ የያዙና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣ የንግድ መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች ለጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/፣ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች አስፈላጊ ሰነዱን አሟልቶ የቴክኒካል እና ፋይናንሺያል በኮፒና ኦርጅናል በማድረግ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 11ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11-04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- 6 ኪሎ አዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ህንጻ ላይ
ስልክ:- 011 154 1475/011 154 19 12
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ
