Tender Detail

Tender Details


የሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ቀለብ እህልና ጥራጥሬ፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ ጽህፈት መሳርያ እና የሥልጠና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ቀለብ እህልና ጥራጥሬ፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ ጽህፈት መሳርያ እና የሥልጠና ዕቃዎች ከነሐሴ 1/2017 . እስከ ኅዳር 30/2018 . 120 ቀናት ከሚያቀርቡ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች፣ አቅራቢ ነጋዴዎችና ማኅበራት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች፡-

1/ በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ

2/ ተጨማሪ ዕሰት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3/ የጨረታው ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 50000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በጥሬ በባንክ የተረጋገጠ ሲፕኦ በማስያዝ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችል፤

4/ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ያለውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5/ ጨረታው 16ኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ላይ ታሽጎ 830 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ሎች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።

6/ ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የመንግስት ሥራ ሰዓት ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል።

7/ የጨረታው አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በራሱ ወጪ ለማሻ /ተቋም ማስረከብ የሚችል፣

8/ ተጫራቾች አሁን ባቀረቡት ዋጋ 4 ተከታታይ ወር ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በመሀሉ የድርድር ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፣

9/ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፤

10/ ተጫራቾች ህጋዊ መጋዘን ቸው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11/ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

የሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም

 

Save Tender