የስልጤ ወረዳ ፋይናንስ Canon 5D mark lV ካሜራ ከነሙሉ መሸከሚያው በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የስልጤ ወረዳ ፋይናንስ Canon 5D mark lV ካሜራ ከነሙሉ መሸከሚያው በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡-
- ተጫራቾች በንግድ ዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ቫት የተመዘገቡበት ሰርተፊኬት ማስገባት፣
- ቲን የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ፣
- በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ፣
- 2% ለመንግስት ግብር እንደሚቆረጥ ማወቅ አለባቸው።
- ግዥው ለእቃው በሰጡት ዋጋ ማቅረቢያ መነሻ በተናጠል ወይም በጥቅል የሚፈፀም መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ዶከመንቶቹን ስ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በማቅረብ በነጻ መውሰድ ይችላሉ።
- ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀኑ ከቀነ 8፡30 ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡45 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል።
- አሸናፊው ድርጅት እቃውን እስከ ስልጢ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ አለበት።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ እስከ አንድ ወር ድረስ ለመስሪያ ቤቱ የማቅረብ ግዴታ አለበት። መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- በጨረታ አሸናፊነት ከተገለፀበት እስከ 7 ቀናት ውስጥ ውል ባይገቡ ያስያዙት ሲፒኦ ውርስ ተደርጎ የተሻለ ግዥ ዘዴ የምንጠቀም መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 046 882 0005/32 ይደውሉ
በማዕ/ኢት/ክ/መንግስት የስልጤ ዞን የስልጤ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
