የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሀዲያ ባህል ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል ለማከበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመከራየት ይፈልጋል፡-
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሀዲያ ባህል ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል ለማከበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመከራየት ይፈልጋል፡-
በዚሁ መሠረት፡-
- ሱት 1- የሀዲያ ብሔር ባህላዊ ልብስ
- ሱት 2- የሙዚቃ መሣሪያ እና ሳውንድ ሲስተም ከነሙሱ አስቴጅ
- በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያለው
- የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው ድርጅቶች
ሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል እንድትወስዱና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1- 30,000 ሎት 2- 30,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ መምሪው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁ 0910432170 መጠየቅ ይቻላል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Open tender for purchase and rental of items for Hadiya cultural New Year celebration: Lot 1 traditional Hadiya clothing; Lot 2 musical instruments and sound system with stage. Bidders need valid trade license, tax ID, VAT registration, and supplier certificate.
