የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- ጣበስፋ / ብግጨ /01/2017/2018
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
ሎት 1 ለተለያዊ ማሽኖችት የሚውሉ ጎማ፣ ኢነር ቱብ፣ ፍላፕ
ሎት 2. የሞተር ሳይክል መለዋወጫ፣
ሎ1-3. የቶዮታ ደብልና ሲንግል መኪና መለዋወጫ፣
ሎት 4. የኒሳን ዩዲ መኪና መለዋወጫ፣
ሎት-5. የተለያዩ ማሽኖች መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በተጫራቹ ድርጅት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000057735167 በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ስም በመክፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ.4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡
ጣና በስስ ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ
ሶስት ቁጥር ማዞሪያ /ቶታል/ ፊት ለፊት ፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ግራውንድ ላይ
ስልክ ቁጥር 011-558-6725
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው።
- ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-5-58-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
