Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 220 4516
  • Website
  • Deadline26 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • opening date2025-08-26 00:00:00
  • Categories Pharmaceutical Products

በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ በ2017 ዓ.ም በሪስቶር ፕሮጀክት በጀት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የተለያዩ ለወጭ ጥገኛ መከላከልና ቁጥጥር አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች እና የውጭ ጥገኛ መድሃኒት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ 2017 . በሪስቶር ፕሮጀክት በጀት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የተለያዩ ለወጭ ጥገኛ መከላከልና ቁጥጥር አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች እና ጥገኛ መድሃኒት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ቁጥር፡- እዓሀቢ 129/2017 የተለያዩ ለወጭ ጥገኛ መከላከልና ቁጥጥር አገልግሎት መገልገያ ግብዓቶች ግዥ

 

የእቃው ዝርዝር

ሎት 1 - የወጭ ጥገኛ መድሃኒት

ሎት 2 - የተለያዩ ለወጭ ጥገኛ መከላከልና ቁጥጥር አገልግሎት የሚውሉ

 

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና መድሃኒቱን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ለማቅረብ መድሃኒትና መኖ አስተዳደር ባለስልጣን የሰጠውን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የሚገዙ ግብዓቶች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የአብከመ ግብርና ቢሮ ቁጥር 69 የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የመወዳደሪያ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሰረት በእያንዳንዱ እቃ ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።
  6. ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናሻል ፕሮፖዛል) እያንዳንዱን ለየብቻው ታሽጐ መቅረብ ይኖርበታል።
  7. ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ መታሸግ ያለባቸው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የሚያረጋግጥ የምስ ወረቀት ማስረጃ፤ የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀናት አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በስንት ቀን ውስጥ እቃውን አጠቃሎ ማስረከብ ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ጽሁፍ።
  8. ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ ማሸግ ያለብዎት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብቻ ነው
  9. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-2-20-45-16/058-2-20-64-79 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ 16ኛው ቀን 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
  11. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058-2-20-45-16 ወይንም 058-2-20-64--79

 

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ

 

Save Tender