የዲላ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በዲላ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤት አገልግሎት የሚውል አላቂ ዕቃ ግዥ በቀረበው ዝርዝር መሠረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የአላቂ ዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
የዲላ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በዲላ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤት አገልግሎት የሚውል አላቂ ዕቃ ግዥ በቀረበው ዝርዝር መሠረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በንግዱ ሥራ ዘርፍ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የንግድ ምዝገባ ም/ወረቀት ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ም/ወረቀት ያለው፣
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ በባንክ የተረጋገጠ የ100,000 /መቶ ሺህ ብር/ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 6 ቀርበው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ዘግይቶ የመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል 1 ኦርጅናል 2 ቴከኒካል ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ፋይናንሻል 1 ኦርጅናል እና 2 ፋይናንሻል ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በማሸግ በመጨረሻ ሁሉንም በአንድ እናት በኤንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም በማድረግ አድራሻቸውን በመሙላት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት
