የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችና አገልግሎት ለ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር - ት/ቢ/ግ/ጨ/-01/18
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችና አገልግሎት ለ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የጽ/መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- የመስተንግዶ አገልግሎት
በመሆኑም፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ
- ተጫራቾች ከዘመኑ ግብርና ታክስ ዕዳ ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ታርጫ ከተማ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በኢን.ባ. በቢሮው ሂሳብ ቁጥር 1000453714528 በማስገባት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በካሽ ፣ ከታወቀ ባንክ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀን ቢድ ቦንድ የባንክ ዋስትና
- ለጽ/መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
- ለመስተንግዶ አገልግሎት ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው።
- የሁለቱም አሸናፊ ተጫራቾች እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም. ድረስ አቅርቦት ለመፈጸም ውል መግባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ህጋዊ የንግድ ማስረጃ ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እና ሌሎች ቴክኒካል ሰነድ ዋናና ኮፒ ለየብቻ በሁለት ፖስታ ፣ የዋጋ ፖስታ ዋናና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- የጽ/መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ጨረታ የእያንዳንዱን ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡ እንዲሁም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክልሉ ትምህርት ቢሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- በመክፈቻው ዕለት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ -በስልከ ቁጥር 0473450715 መጠየቅ ይችላሉ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
