በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2018 የበጀት አመት ለማሰልጠኛ የሚሆኑ መሣርያዎች፣ የፅህፈት መሳርያዎች፣ የህንፃ መሣርያዎች፤ የደንብ ልብስ ፤ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችበግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2018 የበጀት አመት ለማሰልጠኛ የሚሆኑ መሣርያዎች፣ የፅህፈት መሳርያዎች፣ የህንፃ መሣርያዎች፤ የደንብ ልብስ ፤ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችበግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፦
1. የዘርፉን ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፡፡
2. በፌደራል ወይም በክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የቲን ነምበር እናየተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል፡፡
4. ተጫራቾች ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ማካተት አለማካተታቸውን መግለጽ አለባቸው፡፡
5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፕስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በጮሌ ቴ/ ሙ/ት/ስልጠና ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተጠቀሰው ቀናትና ቦታ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ15ኛውቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛኑ ዕለት ከሰኣቱ 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች ካቀርበው ዋጋ የጨረታ መስከበሪያ ብር 5000/አምስት ሺ ብር/ ብቻ በባንከ የተረጋገጠ (CPO) በጮሌ ቴ/ሙ/ት/ ስልጠና ኮሌጅ ስም ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በእጅ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
9. ተሸናፊ ተጫራች ለጨረታ ያስያዘውን ብር ወዲያውኑ ይመለስለታል፡፡
10. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ ወጪ ጮሌ ወረዳ ቴ/ሙ/ት/ ስልጠና ኮሌጅ መቅረብ አለበት፡፡
11. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር፡ - 0927238492/ 0932113459/ ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአርሲ ዞን ጮሴ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ
