Tender Detail

Tender Details

  • Company ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር
  • Address ሀዋሳ ከተማ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በ በሚገኘው ዳዬ በንሳ ሕንጻ 4ተኛ ፎቅ, ቢሮ ቁጥር 12: ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0943027779
  • Website
  • Deadline08 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-09-08 00:00:00
  • Categories Stationery Materials

ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር እና እህት ድርጅቶች የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ዕቃ ለመግዛት የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ዳዬ በንሳ ቢዝነስ /የተወሰነ የግል ማህበር እና እህት ድርጅቶች የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሙሉ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነድ ያገኛሉ።

በዚህም መሠረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መረጃዎች፡-

1. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡና በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የግብርከፋይ መለያ ቁጥር በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈበትን ከገቢዎች ሚኒስቴርየተሰጠ ክሊራንስ ወይም የድጋፍ ደብዳቤ እና በግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የአቅራቢነት ማስረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትንና እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆኑን መገለጽ አለበት፡፡ የታከስ ሁኔታ ያልተገለፀ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጪ አካቶ እንደተሞላ ይቆጠራል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር 10,000 ብር(አስር ሺህ ብር) በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ፋይናንሺያል ኦርጅናል ሰነድ ፖስታ ውስጥ አብረው በማካተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በሀዋሳ ከተማ በገብርኤል ቤተከርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው ዳዬ በንሳ ህንጻ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥርዘወትር በስራ ሰአት መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 220 እስከ 430 ድረስ በቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን አስገብተው ጨረታው በዕለቱ 500 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

7. ተጫራቾት የሚያቀርቡት ዋጋ ቢያንስ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚሆን መሆኑን መገንዘብ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም የፋይናንሺያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

9. ስርዝ ድልዝ ያለው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ከጨረታም ያሰርዛል፡፡

10. የመ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: አድራሻ፦ /አበባ ሮቤራ ቡና ፊት ለፊት በሚገኘው ፒስታ መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ ዳዬ በንሳ ቢዝነስ /የተ/የግል ማህበር

ለበለጠ መረጃ፡- ስልከ ቁጥር 251 116675551/0944350296

ዳዬ በንሳ ቢዝነስ /የተወሰነ የግል ማህበር

Save Tender