ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት
በድጋሚ ጨረታ የወጡ የእቃ/የአገልግሎት ግዥ
ሎት 1 የፈረንጅ እንቁላል አቅርቦት ግዥ
ሎት 2 የወተት አቅርቦት ግዥ
ሎት 3 የማር ጠጅ አቅርቦት ግዥ
ሎት 4 የጤፍና የሩዝ አቀርቦት ግዥ
ሎት 5 የሥጋ አቅርቦት ግዥ
ሎት 6 የአይብ አቅርቦት ግዥ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም. ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ክሊራንስ ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺ ብር/ እና ለሎት 1፣ ለሎት 2፣ ለሎት 3፣ ለሎት 4 እና ለሎት 6 የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቀርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ ኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት፡፡ ተጫራች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መግለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋሰትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መግለጽ አለበት፡
- ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር መጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መስረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማ /ድርጅታዊ ብቃት/ ግምገማ ለሎት 1፣2፣3፣4 እና ለሎት 5 ቴክኒካል ግምገማ ውጤት 60% እና የፋይናንሽያል /ዋጋ/ ግምገማ ውጤት 40% ሲሆን እንደዚሁም ለሎት 6 ቴክኒካል ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት 40% እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት 60% ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ጥራት ግምገማ ሠነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 011-5-53-07 67/011 5 15 73 37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
