Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ
  • Address ኦሮሚያ:ኢትዮጲያ, Phone: 0335540364
  • Website
  • Deadline10 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • opening date2025-09-10 00:00:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Spare Parts

በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ ቁርጥራጭ እና ያገለገሉ የብረት አይነቶች፣ ቁርጥራጭአልሙኒየሞች፣ የተቀየሩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ካዝናዎች፣ የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ጀነሬተሮች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የተለያዩ ቁርጥራጭ እና ያገስገሱ ብረታ ብረቶችን ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፦ ብረታ ብረት ሽያጭ 001/2018 ዓ.ም

በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ ቁርጥራጭ እና ያገለገሉ የብረት አይነቶች፣ ቁርጥራጭአልሙኒየሞች፣ የተቀየሩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ካዝናዎች፣ የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ጀነሬተሮች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. ብረታ ብረቱን ተጫርተው መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ቁርጥራጭ ብረታብረቱ በሚገኝበት መጋዘን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡30-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት 7፡30-11፡30 ሰዓት የከምችቱን ሁኔታ በአካል በመቅረብ ማየት ይቻላል።

3. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር ብቻ/በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡30 እሰከ 11፡30 ሰዓት ከኦሮ/ብሄ/አስ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋና /original/ የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ያለ ስርዝ ድልዝ በመሙላት በፖስታ ማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. በግልፅ የማይነበብ ትከከለኛውን የዋጋ አቀራረብ ስነ ስርዓት ያልተከተለ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ የሚደረግ ሲሆን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ካለ የተጫራቾች አጭር ፊርማ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

7. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በመሙላት ሰነዳቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ የብረታ ብረት ሽያጭ ጨረታ ቁጥር 001/2018 በማለት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ አስራ አምስት ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ ስድስተኟው ቀን በ4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 003 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ ስድስተኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 02 ይከፈታል። አስራ ስደስተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን ይሆናል።

9. አሸናፊው ተጫራች ውል ሲፈርም የውል ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 10% ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡

10. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

 

11. ጨረታውን አሸናፊ የሆነ ድርጅት /ግለሰብ/ ብረታ ብረቱን ወደ ሚፈልግበት ቦታ በራሱ የሚጓጉዝ ይሆናል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 325 KM ላይ ከሚሴ ከተማ እንገኛለን።

ስልክ ቁጥር፡- 033-5-54-03-64/ 033-5-54-02-59/ 033-5-54-21-19 ላይ በመደወል ማንኛውም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

Save Tender