በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደ/3 ሆ/ል ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ንብረቶችን /እቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር A-01/2018
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደ/3 ሆ/ል ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ንብረቶችን /እቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘርፉ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፍቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የቫት ሰርተፍኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN No/፤ ጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች የተሰጠ ደብዳቤ እና የወሩ መጨረሻ ለመንግስት ቫት ሪፖርት የተደረገበት ማስረጃ ሁሉም ማስረጃዎች ንግድ ፍቃዶች በተናጠል ኮፒ ተደርጎ በሌላ ፖስታ መታሽግ አለባቸው፤ የአንዱን ጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 250.00 /ሁለት መቶ ሀምሳ ብር / ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ባህርዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ደ/3 ሆ/ል መኮድ ካምፕ ግዥ ቢሮ ቁጥር-19 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND: CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና GARANTE ማስያዝ አለበት
- የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎች ብር 5,999.90
- የተለያዩ የታካሚ ቀለብ አይነቶች ብር 273,892.16
- የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች ብር 29,086.29
ጨረታው ከእሁድ ነሃሴ 18/2017 እስከ ቅዳሜ ጳጉሜ 01/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ተሽጦ የሚያልቅበት ቀን ሲሆን ሰኞ ጳጉሜ 03/2017 ዓ/ም ጠዋቱ ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 3፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰ/ምዕ/ዕዝ ደ/3 ሆ/ል ትንሹ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በቅደም ተከተል ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ላይ ያልተገለፁ ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፈለጉ ቅፅ 1 ጥር 1998 ዓ/ም በአገር ውስጥ ለሚፈፀሙ እቃዎችና ተዛማጅ አገልግሎቶች ግዥ የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት ግዥ ኤጀንስ ድረ ገፅ ላይ ወይም ከመስሪያ ቤቱ በሚገዙት መደበኛ የጨረታ ሰነድ ማየት ይችላሉ።
የሰሜን ም/ዕዝ ደ/3 ሆ/ል
ስ.ቁ:-058 321 46 98
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደ/3 ሆ/ል
