በአብክመ የኦሮሞ/ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- የልዩ ልዩ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ አቅርቦት ለአንድ ዓመት የሚቆይ እና ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ዘይትና ቅባቶችን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-002/2018 ዓ.ም
በአብክመ የኦሮሞ/ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡-
- የልዩ ልዩ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ አቅርቦት ለአንድ ዓመት የሚቆይ፤
- ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ዘይትና ቅባቶችን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማለትም በተራ ቁ. 1 ለተገለፀው ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በተራ ቁጥር 2 ለተገለጸው ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋናው /original/ የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እሰከ 15ኛው ቀን ከሰኞ እስከ ዓርብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ድረስ በኦሮሞ ብሄ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጂ /original and copy/ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ4፡01 ሰዓት ተዘግቶ 4፡ 30 ሠዓት በግልጽ ይከፈታል። የመከፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ጨረታውን በነጠላ ዋጋ ወይም በጥቅል ዋጋ /ሎት/ የሚያወዳድር መሆኑን እናሳውቃለን።
7. የጨረታ ውጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
8. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
9. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 325 KM ላይ ከሚሴ ከተማ እንገኛለን።
ስልክ ቁጥር፡- 033-5-54-21-19 እና 033-5-54-02-59 ላይ በመደወል ማንኛውም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ የኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ
