ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ለህፃናት ትምህርት ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ የሚያግዙ ልዩ ልዩ የፅህፈት መሳሪያዎች እና ቁሳቁሶችን ለመግዛት አቅዷል በመሆኑም በፅህፈት መሳሪያዎች እና የትምህርት ግብዓቶች አቅርቦት ዘርፍ የተሰማራችሁ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ከ ችልድረንስ ኢን ክሮስ ፋዬር /CiC/ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 9 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ "Pathrway to learning, an Integrated School Readliness Program የተሰኘ ትኩረቱን በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ያደረገ ፕሮጀክት እየተገበርን እንገኛለን ። በመሆኑም ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ለነዚህ አጋር ትምህርት ቤቶች የጨዋታ ተኮር የማስተማር ስነ ዘዴን ለማገዝ እና የሞዴል መማሪያ ክፍሎች ለማደራጀት እና ለህፃናት ትምህርት ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ የሚያግዙ ልዩ ልዩ የፅህፈት መሳሪያዎች እና ቁሳቁሶችን ለመግዛት አቅዷል፡፡ በመሆኑም በፅህፈት መሳሪያዎች እና የትምህርት ግብዓቶች አቅርቦት ዘርፍ የተሰማራችሁ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የቲን ቁጥር ምዝገባ ሰርተፍኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ሰርተፍኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣
- ቁሳቁሶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ስቶርማድረስ የሚችሉ፣
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከድርጅታችን የጨረታ ሰነዱን በነጻ በመውሰድ የፅህፈት መሳሪያዎቹን እና ቁሳቁሶቹን የምታቀርቡበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባትና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ አለም ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፡- 0982882826
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርባችኋል፡፡ በትክክል ካልተገለጸ ቫት እንደተካተተ ተደረጎ ይቆጠራል፡፡
- ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ማስታወቂያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/
