በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ የጽ/መሳሪያ 8,000 ብር፣ 2ኛ የመኪና እቃ መለዋወጫ 10,000 ብር፣ 3ኛ የእንስሳት መድሃኒት 15,000 ብር 4ኛ የፕሪንተር ቀለም 6,000 በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፣
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ የጽ/መሳሪያ 8,000 ብር፣ 2ኛ የመኪና እቃ መለዋወጫ 10,000 ብር፣ 3ኛ የእንስሳት መድሃኒት 15,000 ብር 4ኛ የፕሪንተር ቀለም 6,000 በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፣ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንድሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና አርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተዘረዘረው ሎት የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ከሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቹ በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሽገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች ዕቃውን በሚ/ወ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች ባሉት ንብረት ክፍል ውስጥ ማድረስ ይኖረባቸዋል፡፡
- የጨረታ ውድድሩ እንደአስፈላጊነቱ በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊሆን ይችላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ሆኖ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 011-1-17-01-71 ወይም 09-13-57-44-40 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
