በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለሚገኙ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የብረታ ብረት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለሚገኙ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ተጫራች የብረታ ብረቶቹ በሚገኙበት የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የሚገኙበትን ሁኔታ በመመልከት መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ አላማ በተዘጋጃ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚገዙት እቃ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ባንክ ማረጋገጫ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ ክፍያ እንደፈጸሙ የሚመለስ ይሆናል ለተሸነፉት ተጫራቾች ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቹ በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ የውል ስምምነት ከተፈረመበት ቀን በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ለሚ/ወ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ከከፈለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን እቃ ማንሳት አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስ/ቁ፡- 011-1-17-01-71 ወይም 09-13-57-44-40 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
