Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን
  • Address አ/አ አራዳ ክፍል ከተማ (ፒያሳ) ልዩ ስሙ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው የኢትዮጵያ ስታቲስቲካል አገልግሎት ቢሮ አካባቢ እስጢፋኖስ መካሻ አማረ (EMA ) ህንፃ 9ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 562 2343
  • Website
  • Deadline25 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-09-26 00:00:00
  • Categories Consultancy Service , Cloth And Shoes

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር /////እቃ/ግ/ጨ/02/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት ቁጥር

 

የሚገዛው የእቃ ዓይነት

 

ምርመራ

 

1

የፓሪ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጫማ

720,000.00

2

የፓሪ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የደንብ ልብስ

1,000,000.00

3

የፓራ ሚሊተሪ አፊሰሮች የተለያዩ ትጥቆች

200,000.00

4

የምክር አገልግሎት

14,000.00

 

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-

1.በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፣

4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን TIN ማቅረብ የሚችሉ፣

5. የአቅራቢነት ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፣

6. ወታደራዊ ጫማ በማቅረብ 10 ዓመት እና ከዚያ በላይ ልምድ ያለው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የእራሱ ማምረቻ ፋብሪካ ያለው

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ 230 1100 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፋይናንስ ዳይሬከቶሬት 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08/15 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴከኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናሻል ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻው በማቅረብ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ተከታታይ የስራ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ግዥና ንብረት ///ዳይሬከቶሬት 9 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09/22 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

 

9. የሚቀርበው ዋጋ ማቅረቢያ ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም። ናሙና የተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።

10. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 330 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 400 ሰዓት ይከፈታል።

11. ተጫራቾች በሚጫረቱበት እያንዳንዱ እቃ ጥራት በቴከኒከ ብቃታቸው ከተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል።

12. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

13. /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- / አራዳ ከፍል ከተማ (ፒያሳ) ልዩ ስሙ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው የኢትዮጵያ ስታቲስቲካል አገልግሎት ቢሮ አካባቢ እስጢፋኖስ መካሻ አማረ (EMA) ህንፃ 9 ፎቅ፣ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115622343 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደምብ ማስከበር ባለስልጣን

Save Tender