በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ለጀነሬተር እና ለተለያዩ ሞተር ሳይክሎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/2017-2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት 1 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 2 ለጀነሬተር እና ለተለያዩ ሞተር ሳይክሎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የሃገዢው መጠን ከብር 200.000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራትን ስም፡ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጨረታ ሰነድ ጋር መያያዝ አለበት፤
- ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለጀነሬተር እና ለተለያዩ ሞተር ሳይክሎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር/፣ እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 30,000 /ሰላሳ ሺ ብር/ በባንከ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 - 6 የተጠቀሰትን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/እስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-3300112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት እንገልፃለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
