ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለሚገነባው ለፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅር/ፍ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውል የአርምስትሮንግ ሲሊንግ አቅ/ገጠማ እና አኳስቲከ ሲሊንግ አቅርቦትና ገጠማ ስራ ህጋዊና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 07/2018
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለሚገነባው ለፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅር/ፍ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውል የአርምስትሮንግ ሲሊንግ አቅ/ገጠማ እና አኳስቲከ ሲሊንግ አቅርቦትና ገጠማ ስራ ህጋዊና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
-
ዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፣
-
የጨረታ ማስከበሪያ ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም / unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
-
የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፣
-
የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ድረስ ብቻ ባ/ዳር ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእለቱ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ውድድሩ በሎት /በጥቅል⁄ ዋጋ የሚታይ ሲሆን አስፈላጊ ከሆነና ለኮርፖሬሽኑ ጠቀሚ /አዋጭ/ ሆኖ ከተገኘ በእያንዳንዱ ወይም በነጠላ ዋጋ በማወዳደር አሸናፊው ሊለይ ይችላል፣
-
ተጫራቾች ከአሁን በፊት በዘርፉ ለመስራታቸው የሚያረጋግጥ ለሚወዳደሩበት ዘርፍ የአቅርቦትና ገጠማ ስራ በመስራት የመልካም ስራ አፈጻፀም ስራውን ሰርተው /ገጥመው ካጠናቀቁበት ህጋዊ ተቋም የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
-
ዝርዝር የጨረታ መመሪያው እና የውል ይዘቱ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለባቸው፡፡
-
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር ባህር ዳር -058-218-0538,/09-13-45-41-10/09-18-77-43-12/ አዲስ አበባ :- 011-126-5652/-126-5145/0918705036
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
