የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ግዢ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሀ. ሎት-1 የምግብ ቁሳቁስ (0.6 ሊተር የታሸገ ውሃ፣ ዳይጄስቲቭ ብስኩት እና የህፃናት ወተት)
ለ. ሎት-2 ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች (የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ/Sanitary Pad)
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑ የመንግስት ግብር የከፈሉ ወይም የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያደሱ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና የግብር መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አንዱ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚያሳግድ ይሆናል።
- ተጫራቾች ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ለሚጫረትበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በCPO ወይም ባንክጋራንቲ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት (15) የስራ ቀናት ውስጥ ጨረታ ሰነዱን በጉርድ ሾላ ሳሊተ ምህረት ቤ/ክያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ ከሚገኘው ከኢትዮጽያ ቀይ መስቀል ማኅበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በብር (600) ብር (ስድስት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዳችሁን እስከ ሰኞ መስከረም 26/ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራች ጨረታውን አሸንፎ ባቀረበው ሰነድ መስረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም።
- ጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶች ማለትም ቴክኒካል ዋናውና ኮፒ እና ፋይናንሻል ዋናውና ኮፒ ዶክመንት በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚህ በተዘጋጃው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቁሳቁሶች የአገልግሎት ጊዚያቸው አንድ አመትና ከዚያ በላይ መሆን ያለበት ሲሆን ለዚህም ለሚያቀርቧቸው ቁሳቁሶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተጫራጮች የሚያቀርቡትን ዋጋ ሳይቀይሩ በትእዛዙ መጠን እስከ 25 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
- ጨረታው ሰኞ መስከረም 26/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 በጉርድ ሾላ በሚገኘዉ ሳሊተ ምህረት ቤ/ክያን ፊት ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ በሚገኘዉ የማህበሩ መሰብሰቢያ አደራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር
አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር: 011-515-06-08
ፖስታ ሳጥን ቁጥር: 41076
