Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara National Regional State Education Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-2-26-62-67
  • Websitehttps://anrseb.gov.et/
  • Deadline15 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-10-15 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ተሸከርካሪዎች ላይ የሚገጠም GPS እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጨ-4/2018 ዓ.ም

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ተሸከርካሪዎች ላይ የሚገጠም GPS እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. ጨረታው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀናት ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ከገንዘብ ያዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 13/15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ _ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠም GPS እቃ 50, 000/ሀምሳ ሺህ ብር/ እቃ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮ ህጋዊ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ15 ቀናት እና በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል፡፡

9. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በ4፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከፍል ጨረታው ይከፈታል፡፡

10. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

11. የጨረታ ሰነድለመግዛት ስትመጡ በቢሮው አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክቁጥር 1000012857253 ወይም አባይ ባንክ ቁጥር 2012116113625016 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ የምትወስዱ ይሆናል፡፡

12. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብክመ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከፍል በግንባርበመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላከ ወይም በስልክ ቁጥር058-2-26-62-67/058-3-20-39-99 በመደወል ማግኘት ይቻላል::

13. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

Save Tender